Citizen’s Charter

የኢፌዲሪ ኤምባሲ-ካምፓሊ
የዜጎች ቻርተር ይዘት
1. የቻርተሩ ዓላማ
 የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣
 ለዜጎች ጥራት ያለው አገሌግልት ለመስጠት፣
 ተጠያቂነትን በግልጽ ለማመለከት፣
 ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ያህሌ ፍጥነት ለማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፣
 ዜጎች በኤምባሲው አገሌግልት አሰጣጥ ሊይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት፣ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጥበት ሁኔታ ለማመቻቸት፣
2. ራዕይ
 የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበርና ሌማት በማፋጠን ከዜጎች ጋር የተጠናከረ ግንኙነት ያለው ተቋም መሆን፤
3. ተልዕኮ
 አገራችን ኤምባሲው ከተወከለባቸው አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ሀብት በማስተዋወቅ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ጋር ጠንካራ ትስስር እንዲፈጥሩ መስራት፤
4. ዕሴቶች
 የህዝብ አገልጋይነት – Public Service
 አጋርነት – Partnership Effectiveness
 ተዓማኒነት – integrity
 ሙያዊ ልቀት – Professional

ቁርጠኝነት – Commitment
 ውጤታማነት – Excellence ናቸው
የዕሴቶች መግለጫ
1. የህዝብ አገሌጋይነት (Public Service)
ዜጎችና ባለድርሻ አካላትን በከፍተኛ ትህትና፣ ቅንነትና ቅሌጥፍና ማገልገል ኃሊፊነታችንና ግዳታችን ነው፡፡ ይህም በየዕለቱ በምናደርገው ዲፕልማሲያዊ ተግባራችንን ይገልጻል፡፡ ይህ እሴታችን ደንበኞቻችንና ተጠቃሚዎች በምናስገኘው የእርካታ መጠን፣ እንዲሁም እያንዳንዱን አገልግሎት ለመስጠት ከወሰድነው ጌዜና ጥራት አንፃር የሚለካና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
2. አጋርነት (Partnership)
እንደ ተቋምና እንደ ግለሰብ የኤምባሲው ተልዕኮና ራዕይ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የኤምባሲው ሰራተኞች እርስ በርሳችን እንዲሁም ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላትና የልማት አጋሮች ጋር በምንፈጥረው ወዳጅነትና የተቀናጀ አሰራር አጋርነትን እናጎልብታለን፡፡ አጋርነት የዕለት ተዕለት ስራችን መገለጫ ሲሆን ይህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራዕይ እና ተልዕኮ በማሳካት ሂደት ባፈራናቸው አጋሮች ብዛት የሚለካ እሴት ነው፡፡
3. ተዓማኒነት (integrity)
ለመንግስት ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጥብቅና በመቆም በታማኝነትና በቁርጠኝነት መፈጸም፣ የሀገርንና የዜጎችን ጥቅም በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ማስጠበቅ እንዲሁም የአገርንና የኤምባሲውን ምስጢሮች መጠበቅ፣ ከአድልዎ የጸዳ ግልጽ አሰራር መዘርጋት ፍትሃዊነት፣ ቅንነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ አኳኋን የኤምባሲውን ተልዕኮና ኃሊፊነት በብቃትና ውጤታማነት መወጣትን ይመለከታል፡፡ ይህም የኤምባሲው የስራ ዕቅድችና ግቦችን ከመተግበርና ከማሳካት አኳያ የሚለካ ይሆናል፡፡
4. ሙያዊ ህለቀት (Professional Excellence)
የዲፕልማሲ ስራዎቻችንን በከፍተኛ መያዊ ብቃትና ክህሎት ማከናወንና ይህንንም በዕለት ተዕለት በምንፈጽማቸው የስራ ውጤቶች ጥራት እንዲለካ ማድረግ፣ የኤምባሲው ተልዕኮ ለማሳካት በየጊዜው በዕቅድች አፈፃፀምና ኤምባሲው በሚከታተሏቸው አገራት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የመረጃ ልውውጥ መድረኮች በማዘጋጀት የዲፕልማቶችን አቅም ማሳደግ፣
5. ቁርጠኝነት (Commitment)

ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የአገራችንን ደህንነትና ሰሊም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መነሳሳት ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም ተቋማዊ ኃሊፊነታችንን ለመወጣት በየደረጃው ለሚካሄድ የዲፕሎማሲ ስራ ቁርጠኛ አቋም መያዝ ከሁለም የሚጠበቅ እሴት ነው፡፡
6. ውጤታማነት (Effectiveness)
የዲፕልማሲ ስራችንንና አገልግሎት አሰጣጣችን በቅልጥፍና ከመስራት ባሻገር ስራዎቻችንና አገልግሎታችንን ጥቅም የሚስጡና ውጤት የሚያስመዘግቡ መሆን ይኖርባቸዋል ፡፡
7. ተገልጋዮች
 በዩጋንዳ፣ በሩዋንዳ፣ ቡሩንዲና DRC የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣
 የዲያስፖራ የልማት ማህበራት፣
 የአገራችን የመንግስት መ/ቤቶችና የግል ድርጅቶች፣
 የውስጥ ሰራተኞች፣
8. አጠቃላይ መርሆዎች
 ቀሌጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ ውጤታማና አስተማማኝ የመረጃ አገልግሎት መስጠት፣
 ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ውጤታማ፣ የፓስፖርት፣ የሰነድ ማረጋገጥ፣ የሊሴፓሴ፣ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የውክልና አገልግሎት መስጠት፣
 ላስቀመጥናቸው እሴቶች መገዛት፣
 ለዜጎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት፣
 ከአድሏዊ አሰራርና ከሥነ-ምግባር ጉድለት የፀዳ አሰራርን መከተል፣
 ለሰጠናቸው አገልግሎቶችና ለወሰናቸው ውሳኔዎች ተጠያቂዎች መሆን፣
 መሌካም ተሞክሮዎች ማስፋት፣
9. የተገልጋዮች መብቶች
 በኤምባሲው የሚሰጡ አገልግልቶችን የመጠየቅና የማግኘት፣
 የተሟላ መረጃ የማግኘት፣
 በፍጥነትና በቅልጥፍና የመስተናገድ፣የተሰጣቸውን አገልግሎት በተመለከተ አስተያየት የመስጠት፣
 ባልተገባ አገልግሎት ቅሬታዎቻቸውን በየደረጃው የማሰማትና ለቅሬታዎቻቸው ምላሽ የማግኘት፣
10. ከተገልጋዮች የሚጠበቅ ግዴታ
 ትክክለኛና ተዓማኒነት ያለው መረጃ አሟልቶ ማቅረብ፣
 ታማኝነት፣
 በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት መስጠት፣
11. የሚጠበቁ ስኬቶች (Outcomes)
 የተፈጠረ ጠንካራ የዲያስፖራ ትስስር፣
 በቢዝነስ ፍሰት የተገኘ ተጨማሪ የውጭ ሀብት፣
 ለዜጎችና ተቋማት የተጠበቁ መብቶችና ጥቅሞች፣
 አመለካከቱ የተስተካከለ፣ ሙያዊ ብቃት ያለው፣ ተልዕኮውን የሚፈጽምና መብቶቹ የተጠበቁለት የሰው ሀይል ፣
 በተሰጠ አገልግሎት የጨመረ የተገልጋዮች እርካታ፣
 ኤምባሲው የተወከለባቸው አገራት ሰለአገራችን ልማት፣ ሰላምና ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ደጋፊ አመለካከት፣
 የተገነባ የሀገር ገጽታና የተበራከቱ ደጋፊዎች፣

Citizen charter